ድል ፡ ነሳ ፡ ሆ! (Del Nesa Ho!)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝድል ፡ ነሳ ፡ ድል ፡ ንሳ ፡ ሆ! (፪x)
ድል ፡ ነሳ ፡ ከሙታን ፡ ተነሣ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ

1. ሰይጣን ፡ በጥቂቱ ፡ ሊያተፋኝ
የመከራን ፡ ናዳ ፡ አውርዶብኝ
በድቅድቅ ፡ ጨለማ ፡ ሆኜ ፡ ሳለሁ
በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ብርሃን ፡ አየሁ

አዝድል ፡ ነሳ ፡ ድል ፡ ንሳ ፡ ሆ! (፪x)
ድል ፡ ነሳ ፡ ከሙታን ፡ ተነሣ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ

2. ሃሳቡ ፡ የተሳካ ፡ እየመሰለው
ጭንቀቴን ፡ ጥበቱን ፡ እያበዛው
ላጠፋው ፡ ነው ፡ ብሎ ፡ ደስ ፡ ሲለው
ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ጉድ ፡ አደረገው

አዝድል ፡ ነሳ ፡ ድል ፡ ንሳ ፡ ሆ! (፪x)
ድል ፡ ነሳ ፡ ከሙታን ፡ ተነሣ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ

3. ሰይጣን ፡ ጉዱ ፡ ፈላ ፡ ምን ፡ ይዋጠው
የሚያቃጥል ፡ እሳት ፡ አጋጠመው
መቼም ፡ የሚገባበት ፡ የለምና
ሰገደ ፡ ላምላኬ ፡ ወደቀና

አዝድል ፡ ነሳ ፡ ድል ፡ ንሳ ፡ ሆ! (፪x)
ድል ፡ ነሳ ፡ ከሙታን ፡ ተነሣ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ

4. ባለው ፡ ጉልበት ፡ ኃይሉ ፡ ተጠቀመ
ጭንቀቴን ፡ ጥበቴን ፡ አራዘመ
ግን ፡ እንደ ፡ ሃሳቡ ፡ አልጐዳኝም
የእስራኤል ፡ አምላክ ፡ አልጠላኝም

አዝድል ፡ ነሳ ፡ ድል ፡ ንሳ ፡ ሆ! (፪x)
ድል ፡ ነሳ ፡ ከሙታን ፡ ተነሣ
ኢየሱስ ፡ ድል ፡ ነሳ