From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
በአምላካችን ፡ ቅጥር ፡ እየዘለልን
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ እየዘለቅን
ጌታችን ፡ ነግሶ ፡ እናየዋለን
1. አውሎ ፡ ነፋስ ፡ ተነስቶ ፡ ብዙ ፡ ቢፈትነንም
ካለንበት ፡ መሠረት ፡ ሊነቅለን ፡ ቢገፋንም
በጥልቁ ፡ ከተተከልን ፡ አያነቃንቀንም
የማዕበል ፡ ሁሉ ፡ አዛዥ ፡ ለእድቀት ፡ አይሰጠንም
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
በአምላካችን ፡ ቅጥር ፡ እየዘለልን
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ እየዘለቅን
ጌታችን ፡ ነግሶ ፡ እናየዋለን
2. ቸነፈር ፡ ረሃብና ፡ የችግር ፡ መፈራረቅ
ዘማዊ ፡ ትውልድ ፡ በዝቶ ፡ ኑሮ ፡ ቢሆን ፡ ትንቅንቅ
ሁሉን ፡ በሚችል ፡ አምላክ ፡ ጥላ ፡ ውስጥ ፡ በእምነት ፡ አድረን
ከኃጢአት ፡ መዘዝ ፡ ተርፈን ፡ ድልን ፡ እናውጃለን
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
በአምላካችን ፡ ቅጥር ፡ እየዘለልን
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ እየዘለቅን
ጌታችን ፡ ነግሶ ፡ እናየዋለን
3. ጦርና ፡ የጦር ፡ ወሬ ፡ ሰምተን ፡ ተደናግጠናል
በደም ፡ መፍሰስ ፡ ምክንያት ፡ እጅግ ፡ በጣም ፡ አዝነናል
ሆኖም ፡ በጸሎት ፡ ተግተን ፡ ጌታን ፡ ተነስ ፡ ብንለው
ቶሎ ፡ ይደርስልናል ፡ እርሱ ፡ የቅርብ ፡ አምላክ ፡ ነው
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
በአምላካችን ፡ ቅጥር ፡ እየዘለልን
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ እየዘለቅን
ጌታችን ፡ ነግሶ ፡ እናየዋለን
4. ያቃተን ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ከእግሮቻችን ፡ ሥር ፡ ወድቆ
ጠላት ፡ ያቆጠቆጠው ፡ በኢየሱስ ፡ ሥም ፡ ደርቆ
በምድር ፡ ዙሪያ ፡ ሁሉ ፡ የወንጌል ፡ እውነት ፡ ገኖ
ገና ፡ እናየዋለን ፡ እግዚአሔር ፡ ታላቅ ፡ ሆኖ
አዝ፦ ድል ፡ በድል ፡ እንሄዳለን
በአምላካችን ፡ ቅጥር ፡ እየዘለልን
ከኃይል ፡ ወደ ፡ ኃይል ፡ እየዘለቅን
ጌታችን ፡ ነግሶ ፡ እናየዋለን
|