ድካም ፡ ይዞኛል (Dekam Yezognal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል
ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል
ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ
እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ

1. ቃልህን ፡ ለማንበብ ፡ ዐይኔ ፡ ታወረ
ሳልጸልይ ፡ ጉልበቴ ፡ ታሰረ
አንተን ፡ እንዳላስብ ፡ አዕምሮዬ ፡ ዛለ
እግሬም ፡ ወደ ፡ ጥፋት ፡ ኮበለለ

አዝ፦ እኔን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ድካም ፡ ይዞኛል
ድምጼንም ፡ ላሰማህ ፡ አቅቶኛል
ወድቄአለሁኝ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ አንሳኝ
እባክህ ፡ ሕይወቴን ፡ ለውጥልኝ

2. ጠፋሁኝ ፡ ጌታ ፡ ካልደረስክልኝ
ዓለም ፡ እንደ ፡ ጐርፍ ፡ እንከባለለኝ
በኀጢአት ፡ ባሕር ፡ ልሰጥም ፡ ነውና
ጌታ ፡ ሆይ ፡ እባክህ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ

አዝ፦ አትጨክን ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ በልጅህ
አውቃለሁኝና ፡ ጉድለቴን
ጌታ ፡ ሆይ ፡ አሁን ፡ ኀጢአቴን ፡ ማረኝ
የምመራበትን ፡ ብርሃን ፡ ስጠኝ

3. አየሁ ፡ ጌታዬን ፡ ወዲህ ፡ ሲመጣ
እኔን ፡ ከጥፋት ፡ ሊያወጣ
እጁን ፡ ላከልኝ ፡ ፍፁም ፡ አዳነኝ
ከእንግዲህስ ፡ ከጌታዬ ፡ ጋር ፡ ነኝ

አዝ፦ ፍፁም ፡ ቸል ፡ አልልም ፡ እርሱን ፡ ስከተል
እኔን ፡ ለመውሰድ ፡ ስለሚያስብ
መስቀሉ ፡ ለእኔ ፡ ቢከብደኝ ፡ እንኳ
ፍፁም ፡ ለመሸከም ፡ አልቦዝንም