ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ ባርከን (Degmeh Degmeh Barken)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ ባርከን ፡ አሁንም (፪x)
እረክተናል ፡ ጠግበናል ፡ አንልም (፪x)
ጽዮን ፡ ስንደርስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ እርካታችን (፪x)
እስከዚያው ፡ ግን ፡ መግበን ፡ አባታችን

2. ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ መግበን ፡ ቃልህን (፪x)
በኛም ፡ ዘመን ፡ ግለጸው ፡ ኃይልህን (፪x)
እንመልከት ፡ ስትሠራ ፡ በፊታችን (፪x)
ኃይሉ ፡ ይቅለጥ ፡ ይሰበር ፡ ጠላታችን

3. ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ አሰማን ፡ ድምጽን (፪x)
ፍጻሜያችን ፡ ያማረ ፡ እንዲሆን (፪x)
ከእውነትህ ፡ እንዳንስት ፡ በጉዟችን (፪x)
ሕያው ፡ ቃልህ ፡ ይሁነን ፡ ምርኩዛችን

4. ደግመህ ፡ ደግመህ ፡ አሳየን ፡ ክብርህን (፪x)
ከእሳት ፡ ከውኃ ፡ አድነን ፡ ሕዝብህን (፪x)
ከእኛ ፡ ጋር ፡ እንዳለህ ፡ በዓለም ፡ ይታይ
አንተም ፡ ክበር ፡ ከፍ ፡ በል ፡ በምድር ፡ ላይ (፪x)