ዳገት ፡ ቁልቁለቱን (Daget Qulquletun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ዳገት ፡ ቁልቁለቱን ፡ አብሮ
እዚህ ፡ ላደረሰኝ ፡ አሻግሮ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታዬን
ድጋፍ ፡ አለኝታዬን (፪x)

ከሚያስፈራው ፡ ሞገድ ፡ ከወጀብ ፡ ከማዕበል
ጌታዬ ፡ ጠብቆ ፡ እዚህ ፡ አድርሶኛል
እስቲ ፡ ላመስግነው
ጌታዬ ፡ ታላቅ ፡ ነው

አዝ፦ ዳገት ፡ ቁልቁለቱን ፡ አብሮ
እዚህ ፡ ላደረሰኝ ፡ አሻግሮ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታዬን
ድጋፍ ፡ አለኝታዬን (፪x)

ለዘመናት ፡ አብረን ፡ ስንጓዝ ፡ ከርመናል
ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ መች ፡ ይተወኛል?
ልቀኝለት ፡ ቅኔ!
ለታማኝ ፡ ወገኔ!

አዝ፦ ዳገት ፡ ቁልቁለቱን ፡ አብሮ
እዚህ ፡ ላደረሰኝ ፡ አሻግሮ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታዬን
ድጋፍ ፡ አለኝታዬን (፪x)

አንጽቶኛልና ፡ ጌታዬ ፡ በደሙ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ከፍ ፡ ላድርገው ፡ ስሙን
የችግር ፡ ደራሼ!
ድጋፍ ፡ ምሰሶዬ!

አዝ፦ ዳገት ፡ ቁልቁለቱን ፡ አብሮ
እዚህ ፡ ላደረሰኝ ፡ አሻግሮ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታዬን
ድጋፍ ፡ አለኝታዬን (፪x)

ከቀኑ ፡ ፍላጻ ፡ ከሌሊቱ ፡ ግርማ
አልብሶኛልና ፡ በመንፈሱ ፡ ሸማ
ልቅረብ ፡ በምሥጋና
ጥላዬ ፡ ነውና!

አዝ፦ ዳገት ፡ ቁልቁለቱን ፡ አብሮ
እዚህ ፡ ላደረሰኝ ፡ አሻግሮ
እስቲ ፡ ላመስግነው ፡ ጌታዬን
ድጋፍ ፡ አለኝታዬን (፪x)