ቸሩ ፡ መድኃኒቴ (Cheru Medhanitie)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ቸሩ ፡ መድኃኒቴ
የመጣ ፡ በፍቅሩ
በዓለምም ፡ ውርደት
ከጥንታዊ ፡ ክብሩ

ፍቅሩም ፡ አደረሰው
በመከራና ፡ ሞት
ሕይወቴን ፡ ለማዳን
ተሸከመ ፡ ቅጣት

አቤቱ ፡ ፍቅርህን
ግለጠው ፡ በላዬ
ብርሃንህን ፡ ስጠኝ
በጨለመ ፡ ልቤ

በጨለማ ፡ ዓለም
ለታሠረ ፡ ነፍሱ
የፀጋ ፡ ዓርነት
ግለጠው ፡ በራሱ