ብሩሕ ፡ ፀሐይህ ፡ ወጥቷል (Biruh Tsehayih Wottitoal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

ብሩሕ ፡ ፀሐይህ ፡ ወጥቷል
ተመስገን ፡ አምላኬ
በአዲስ ፡ ተስፋ ፡ በአዲሥም ፡ ኃይል
ልስገድ ፡ ተንበርክኬ

ለክፉውም ፡ ለፃድቅም
ፀሐይህ ፡ ያበራል
እንዳንተም ፡ ርኅሩኅ ፡ የዋኅም
ልሆን ፡ ይገባኛል

በዚህም ፡ ቀን ፡ ፈቃድህን
ልፈጽመው ፡ እርዳኝ
አሳስበኝም ፡ ሕግህን
በቃልህም ፡ ምራኝ

ወዳባትነትህ ፡ ልሸሽ
በዓይንህ ፡ ጠብቀኝ
ቀንም ፡ ሲብት ፣ ሌትም ፡ ሲመሽ
የአንተ ፡ ገንዘብ ፡ ነኝ