ቤታችን ፡ ፈራሽ ፡ ድንኳን ፡ ነው (Bietachen Ferash Denkuan New)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ለዚህ ፡ ዓለም ፡ ባዕድ ፡ ሆነን
ኢየሱስን ፡ እንጠብቃለን
እዚህ ፡ ዛላቂ ፡ ቤት ፡ የለንም
እርስታችን ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ነው

አዝ፦ ቤታችን ፡ ፈራሽ ፡ ድንኳን ፡ ነው
እስክንሄድ ፡ ከዚች ፡ ዓለም
እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ ቤት ፡ የለንም
እርስታችን ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ነው

በመከራ ፡ በስደትም
አናምርር ፡ አናጉረምርም
ለአጭር ፡ ጊዜ ፡ እንቆያለን
ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ እስኪወስደን

አዝ፦ ቤታችን ፡ ፈራሽ ፡ ድንኳን ፡ ነው
እስክንሄድ ፡ ከዚች ፡ ዓለም
እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ ቤት ፡ የለንም
እርስታችን ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ነው

በአዲሲቷ ፡ ኢየሩሳሌም
እንግዶች ፡ በማንሆንበት
ከጌታ ፡ ጋር ፡ ባለእርስቶች
የተገዛን ፡ የአምላክ ፡ ልጆች

አዝ፦ ቤታችን ፡ ፈራሽ ፡ ድንኳን ፡ ነው
እስክንሄድ ፡ ከዚች ፡ ዓለም
እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ ቤት ፡ የለንም
እርስታችን ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ነው

የግብጻውያንን ፡ አገር ፡ ትተው
እንደወጡ ፡ እስራኤላውያን
እንገሥግስ ፡ እኛም ፡ ወደፊት
ወደ ፡ ሰማይ ፡ የተስፋ ፡ ርስት

አዝ፦ ቤታችን ፡ ፈራሽ ፡ ድንኳን ፡ ነው
እስክንሄድ ፡ ከዚች ፡ ዓለም
እዚህ ፡ ነዋሪ ፡ ቤት ፡ የለንም
እርስታችን ፡ በሰማይ ፡ ቤት ፡ ነው