በዙፋኑ ፡ ፊት ፡ ድነው ፡ የቆሙቱ (Bezufanu Fit Dinew Yeqomutu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በዙፋኑ ፡ ፊት ፡ ድነው ፡ የቆሙቱ
ነጭ ፡ ልብሥም ፡ ለብሰው ፡ ለመድኃኒቱ
ክብር ፡ የሚሰጡቱ
እሊያ ፡ ማን ፡ ናቸው?
እለዚያ ፡ ዳኑ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም
ነጹም ፡ በበጉ ፡ ደም ።

እሊያ ፡ ከታላቅ ፡ ጭንቀት ፡ መጥተው
በበጉም ፡ ደም ፡ ልብሣቸውን ፡ አጥበው
ኢየሱስን ፡ ተቀብለው
የዳኑቱ ፡ ናቸው ።
እለዚያ ፡ ዳኑ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም
ነጹም ፡ በበጉ ፡ ደም ።

ለዘለዓለም ፡ ድነው ፡ ከዚህ ፡ ምድር ፡ ፃር
ደርድረው ፡ የመሰንቆውን ፡ አውታር
አዲስ ፡ መዝሙር ፡ በማይሻር
ደስታ ፡ ያሰማሉ ።
እለዚያ ፡ ዳኑ ፡ በኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ስም
ነጹም ፡ በበጉ ፡ ደም ።