በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዘመን (Bezih Hulu Zemen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አይቸኩልም ፡ ጌታ ፡ አርፍዶ ፡ ይነሳል
ግን ፡ ማንም ፡ አይቀድመውም
በጊዜው ፡ ይደርሳል
ጌታን ፡ ከዙፋኑ ፡ ለማውረድ ፡ የለፉ
ትላንት ፡ የነበሩ ፡ ዛሬ ፡ ግን ፡ የጠፉ
እጅግ ፡ ብዙ ፡ ብዙ ፡ ናቸው
ታዲያ ፡ ምን ፡ ያደርጋል ፡ ሞት ፡ አሸነፋቸው

አዝ፦ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዘመን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነው (፪x)

መቃብር ፡ ጠባቂው ፡ በከንቱ ፡ ሲጉላላ
ኢየሱስ ፡ ተነስቶ ፡ ከተማውን ፡ ሞላ
ዛሬም ፡ ባዶ ፡ ህንጻ ፡ ሰይጣን ፡ ያስጠብቃል
ጌታ ፡ የጓዳውን ፡ ህዝቡን ፡ ያንቃቃል
ግሩም ፡ ነው ፡ ድንቅ ፡ ነው
ዛሬም ፡ ለዘለዓለም ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው

አዝ፦ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዘመን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነው (፪x)

ነብያት ፡ ነን ፡ ባዮች ፡ በስሙ ፡ የነገዱ
የአምልኮ ፡ ምልክ ፡ ይዘው ፡ ኃይሉን ፡ ግን ፡ የካዱ
ስተው ፡ እያሳቱ ፡ ጥቂት ፡ ዘመን ፡ ኖሩ
ቀናቸው ፡ አበቃ ፡ ሞቱ ፡ ተቀበሩ
አለ ፡ በአፈር ፡ አጥንታቸው
በጐልጐታ ፡ ያለው ፡ ባዶ ፡ መቃብር ፡ ነው

አዝ፦ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዘመን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነው (፪x)

እውነት ፡ መሰል ፡ ተረት ፡ ይዘው ፡ የተነሱ
በወሬ ፡ መሰላል ፡ ሰማይ ፡ የደረሱ
ፈጣሪ ፡ አማልክት ፡ መባል ፡ ያማራቸው
ከነፋቄያቸው ፡ ጋር ፡ ምድር ፡ ዋጠቻቸው
ተረታቸው ፡ ወዴት ፡ አለ ፡ እውነተኛ ፡ አምላክ
ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ተባለ

አዝ፦ በዚህ ፡ ሁሉ ፡ ዘመን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ነው
ትላንትናም ፡ ዛሬ ፡ ለዘለዓለም ፡ ያው ፡ ነው (፪x)