በዚህ ፡ በእንግድነቴ ፡ ልቤ ፡ ለምን ፡ ይፈራል (Bezih Beingidinete Libee Lemin Yiferal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በዚህ ፡ በእንግድነቴ
ልቤ ፡ ለምን ፡ ይፈራል?
ያ ፡ ዕሙኑ ፡ መድኃኒቴ
መራመዴን ፡ ይመራል
የሞተው ፡ ስለ ፡ በጐቹ
በቃሉና ፡ በመንፈሱ
ከእኛ ፡ ጋር ፡ ይኖራል ።

እከተላለሁ ፡ ኮቴውን
ድምፁም ፡ ይታወቀኛል
በጐ ፡ እረኛም ፡ በጐቹን
ቆጥሮ ፡ ሁሉን ፡ ያውቃል
የጠፉትን ፡ ይፈልጋል
የደከመውን ፡ ይሸከማል
የወደቀውን ፡ ያስነሣል ።

የሕይወት ፡ ሕብስት ፡ አብልቶ
ከፀጋ ፡ ምንጭ ፡ ያጠጣል
በመንፈስ ፡ ኃይል ፡ አበርትቶ
ሰላሙንም ፡ ይሰጣል
በጨለማ ፡ እንኳ ፡ ብሄድ
እርሱን ፡ ተከትዬ ፡ ስሄድ
አንድ ፡ ቅዱስ ፡ ድፍረት ፡ አለኝ ።

በጌን ፡ በኃይል ፡ ከመንጋዬ
የሚነጥቅብኝ ፡ የለም
ስትል ፡ ኦ! ቸር ፡ እረኛዬ
ና ፡ ጠብቀኝ ፡ ከዓለም
ይህ ፡ ዓለም ፡ በከንቱነት
በእጅህ ፡ ከሚመሩቱ
አይሳበኝ ፡ ለዘለዓለም ።

ይህ ፡ ሕይወት ፡ እንደ ፡ ሕልም ፡ ያልፋል
በርረን ፡ እንሄዳለን
ቀናችን ፡ ይመሽብናል
ከዚህ ፡ እንጓዛለን
ሲያልቅም ፡ እንግድነቱ
እንዳልኸን ፡ ባለህበቱ
እኛም ፡ እንሆናለን ።