በየሰዓት ፡ በየጊዜው (Beyeseat Beyegiziew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

መድህኔ ፡ ተቀበለኝ
እጠጋለሁ ፡ ጌታ ፡ ወዳንተ
ደምህ ፡ እንዲጠብቀኝ
ከመለየት ፡ አምላኬ ፡ ከአንተ

አዝማች
በየሰዓት ፡ በየጊዜው
በደምህ ፡ እኔን ፡ አንጻኝ
በምሕረትህ ፡ አቅርበኝ
በፍቅርህም ፡ እኔን ፡ ሰውረኝ

በዚህ ፡ ዓለምም ፡ ሳለሁ
አንተ ፡ ምራኝ ፡ በመራመዴ
በአንተ ፡ ከታመንኩብህ
አይጠፋኝም ፡ ከቶ ፡ መንገዴ

አዝማች
በየሰዓት ፡ በየጊዜው
በደምህ ፡ እኔን ፡ አንጻኝ
በምሕረትህ ፡ አቅርበኝ
በፍቅርህም ፡ እኔን ፡ ሰውረኝ

ሕይወቴ ፡ እስኪያልፍ ፡ ድረስ
ፍቅሬ ፡ ለአንተ ፡ እንዲጸናልኝ
በፍቅር ፡ እጅህ ፡ ያዘኝ
ወደ ፡ ሰማይ ፡ ቤትህ ፡ አድርሰኝ

አዝማች
በየሰዓት ፡ በየጊዜው
በደምህ ፡ እኔን ፡ አንጻኝ
በምሕረትህ ፡ አቅርበኝ
በፍቅርህም ፡ እኔን ፡ ሰውረኝ