በየሆዋ ፡ ዙፋን (Beyehowa Zufan)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በየሆዋ ፡ ዙፋን ፡ ዙሪያ
እንቅረብ ፡ በደስታ
እዚያ ፡ ከሱ ፡ ሌላ ፡ አምላክ ፡ የለም
ለመፍጠርም ፡ ለማጥፋትም

በሥልጣኑ ፡ ሳንረዳው
ሰውን ፡ ከሸክላ ፡ የሰራው
እንደ ፡ በጐችም ፡ ጠፍተን ፡ ሳል
በደሙ ፡ መልሶ ፡ ገዛን

ቤቱን ፡ በምሥጋና ፡ ሞልተን
ሲያስተጋባ ፡ መዝሙራችን
የምድርም ፡ ነገድ ፡ ሁሉ
እርሱን ፡ ያመሰግናሉ

ትእዛዙ ፡ ለሁሉም ፡ ነው
ፍቅሩም ፡ ዘለዓለማዊ ፡ ነው
እውነቱም ፡ እንደ ፡ ሕንጻ ፡ ነው
ዘመን ፡ ከቶ ፡ የማይሽረው