በፀጋው ፡ እግዚአብሔር ፡ የጠፋውን ፡ ሰው ፡ አዳነ (Betsegaw Egziabher Yetefawun Sew Adane)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በፀጋው ፡ እግዚአብሔር
የጠፋውን ፡ ሰው ፡ አዳነ
ልጁንም ፡ ወደዚች ፡ ምድር
ላከ ፡ ሊያድነነ
ዓለም ፡ በኃጢአት ፡ ብዛት
ሰጥሞ ፡ ጠፍቶ ፡ ነበር
ጽድቅና ፡ ሕይወት
የአምላክ ፡ ልጅ ፡ ባይሞት
ባልተገኘልን ፡ ነበር

ወልድም ፡ በዓለም ፡ ላይ ፡ ሊፈርድ
አልመጣም ፡ ወደ ፡ እኛ
የፍርድ ፡ መዓት ፡ ግን ፡ እንዲበርድ
ተሠዋ ፡ ያለም ፡ ዳኛ
ጠፍቶ ፡ የነበር ፡ ብጽዕናም
ከዓብ ፡ በወልድ ፡ ተሰጠን
ተመለሰልን
በእርሱም ፡ የሚያምን
ይድናል ፡ ለዘለዓለም

በክርስቶስ ፡ ግን ፡ ያላመነ
አሁን ፡ ተፈረደበት
በራሱ ፡ እርሱ ፡ ኮነነ
ጥፋቱም ፡ አይቀርለት
የረገጠ ፡ የወልድን ፡ ደም
ብጽዕናን ፡ አያገኝም
የአምላክ ፡ በግም
ያስፈርድበታል
ሰማይንም ፡ ይነሣል

ጌታችን ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ሆይ!
ነፍስህን ፡ ለወጥህልን
በሞት ፡ ጽላ ፡ እንዳንቆይ
በመስቀል ፡ ላይ ፡ ሞትህልን
ኦ ፡ አምላክ ፡ ፀጋህ ፡ በዝቷል
ኦ ፡ ያምላክ ፡ ልጅ ፡ ተመስገን
በምድር ፡ ሳለን
ምሥጋናህ ፡ አንሷል
በዚያ ፡ ግን ፡ ይደምቃል