በተስፋ ፡ ስቀርበው (Betesfa Seqerbew)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በተስፋ ፡ ስቀርበው ፡ ለመስማት
ቃሉን ፡ ሲያበራልኝ
የጨለማ ፡ ኃይልም ፡ ይርቃል ፡ ከእኔ
የሕይወትም ፡ ብርሃን ፡ ይበራል

በፍቅር ፡ መንፈስ ፡ ይጠራናል ፡ ዛሬ ፡ ሳይቆጣ
ለመንፈሱ ፡ ክፈት ፡ ልብህን ፡ አሁን
በንቃትም ፡ አድምጸው ፡ ቃሉን

እንዴት ፡ ያለ ፡ ተስፋ ፡ ይሰጣል ፡ ዛሬ
ለልጆቹ ፡ አሁን ፡ ያለዋጋ ፡ ይሰጣል
ፅድቁን ፡ ድሆችም ፡ ደግሞ ፡ ያገኛሉ

ከኃጢአት ፡ ባርነት ፡ ለማውጣት ፡ ቶሎ
ለደካሞች ፡ ደክሞነ ፡ ሲኖርም
የኃጢአት ፡ ቀንበር ፡ በፀጋው ፡ ይፈታናል ፡ አሁን