በትዕግሥት ፡ ጸጥታ (Betegest Tseteta)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

የበረታ ፡ ሰልፍ ፡ ሲከበኝ ፡ ከኋላ ፡ ከፊት
ቆይቼ ፡ እግዚአብሔርን ፡ ደጅ ፡ ጠናሁት
እርሱም ፡ ዘንበል ፡ አለልኝ ፡ ሊያዳምጠኝ
እንባዬን ፡ በእጁ ፡ ጠርጐ ፡ ቃሉን ፡ ሰጥቶ ፡ አጽናናኝ

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

ነፍሽ ፡ ስትራቆት ፡ ፍፁም ፡ ባዶ ፡ ስትሆን
ያለህን ፡ አራግፈህ ፡ ዘርተህ ፡ ስታይ ፡ ራስህን
ያሳለፍካቸውን ፡ ድሎች ፡ አስብ ፡ ተስፋህ ፡ ይለምልም
ተንበርክከህ ፡ ብትቆይ ፡ ደግሞ ፡ መዳሰሽ ፡ አይቀርም

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ

ከድካም ፡ የበረቱ ፡ ሰዎች ፡ በድል ፡ ያለፉ
ከኢየሱስ ፡ በስተቀኝ ፡ በላይ ፡ የተሰለፉ
መንግሥታትን ፡ ድል ፡ ነስተው ፡ ያኔ ፡ ምሽግ ፡ የናዱ
የጸሎት ፡ ሰዎች ፡ ናቸው ፡ ጠላት ፡ ያርበደበዱ

አዝ፦ በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
ድል ፡ ይገኛል ፡ ከጌታ
በትዕግሥት ፡ ጸጥታ ፡ በጸሎት ፡ ቆይታ
መልስ ፡ ይመጣል ፡ ከጌታ