በታላቅ ፡ ግርማ (Betalaq Girma)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በታላቅ ፡ ግርማ ፡ በዙፋኑ ፡ ላለው
የምሥጋና ፡ ዘውድ ፡ በራሱ ፡ ለጫነው
እዘምራለሁ (፬x)

እኔ ፡ አፌን ፡ አልከፍትም ፡ ለዓለም ፡ ክብር
እዘምራለሁኝ ፡ ለእግዚአብሔር (፪x)
እቀኝለታለሁኝ ፡ በአዲስ ፡ በአዲስ ፡ ዜማ
የምሥጋናዬ ፡ ድምጽ ፡ በአሪያም ፡ ይሰማ (፪x)

በታላቅ ፡ ጉባኤ ፡ ሰውም ፡ በበዛበት
ለእስራኤል ፡ ቅዱስ ፡ ቅኔ ፡ ልቀኝለት (፪x)
ከንፈሮቼ ፡ እጅግ ፡ እጅግ ፡ ደስ ፡ አላቸው
ምሥጋና ፡ ሲያቀርቡ ፡ ለፈጣሪያቸው (፪x)