በሠርግ ፡ ቀን (Beserg Qen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በሠርግ ፡ ቀን ፡ በደስታ ፡ ቀን
ሙሽሪት ፡ ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ስትሆን
በጉባኤ ፡ በምሥጋና
ጌታን ፡ ስንወድስ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)

ሕዝቡን ፡ የሚያጽናና ፡ የሚደግፍ
ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሞልቶ ፡ የሚያሳርፍ
እንደ ፡ እግዚአብሔር ፡ ያለ ፡ የለምና
ጉባኤው ፡ ያክብረው ፡ በምሥጋና

አዝ፦ በሠርግ ፡ ቀን ፡ በደስታ ፡ ቀን
ሙሽሪት ፡ ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ስትሆን
በጉባኤ ፡ በምሥጋና
ጌታን ፡ ስንወድስ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)

እንደተለመነው ፡ ሁሉን ፡ ሰምቶ
በፍቅር ፡ ደግፎ ፡ ኃይልን ፡ ሰጥቶ
ለወግ ፡ ለማዕረጉ ፡ አበቃችሁ
ሙሽራዎች ፡ እንኳን ፡ ደስ ፡ አላችሁ

አዝ፦ በሠርግ ፡ ቀን ፡ በደስታ ፡ ቀን
ሙሽሪት ፡ ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ስትሆን
በጉባኤ ፡ በምሥጋና
ጌታን ፡ ስንወድስ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)

ሙሽሪት ፡ ሙሽራ ፡ በሠርጋችሁ
ጌታን ፡ አመስግኑ ፡ ከልባችሁ
ጉባኤው ፡ በሙሉ ፡ ጌታን ፡ ያክብር
በአንድነት ፡ ምሥጋናን ፡ ይዘምር

አዝ፦ በሠርግ ፡ ቀን ፡ በደስታ ፡ ቀን
ሙሽሪት ፡ ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ስትሆን
በጉባኤ ፡ በምሥጋና
ጌታን ፡ ስንወድስ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)

እኛም ፡ በደስታችሁ ፡ ደስ ፡ ብሎናል
ምሥጋናን ፡ ለማቅረብ ፡ ተነስተናል
ውዳሴም ፡ ምሥጋና ፡ በዕልልታ
ዙፋኑን ፡ ይክበበው ፡ ይክበር ፡ ጌታ

አዝ፦ በሠርግ ፡ ቀን ፡ በደስታ ፡ ቀን
ሙሽሪት ፡ ከሙሽራው ፡ ጋር ፡ ስትሆን
በጉባኤ ፡ በምሥጋና
ጌታን ፡ ስንወድስ ፡ ደስ ፡ ብሎናል (፪x)