በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ ወዳለበት ፡ ጌታ (Besemayat Besemayat Wodalebet Gieta)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ ወዳለበት ፡ ጌታ
ይታደላሉ ፡ ቅዱሣን ፡ ብፅዕናና ፡ ደስታ
ያያሉ ፡ ጌታን ፡ ፊት ፡ ለፊት
ይዘምራሉ ፡ ቀን ፡ ሌሊት
ለአምላክ ፡ ፀባዖት ።

በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ እንዴት ፡ ያለ ፡ ብርሃን
ከቀን ፡ ፀሐይ ፡ ከፀዳሉ ፡ የደመቀ ፡ ዙፋን
ያ ፡ ከቶ ፡ የማያልቅ ፡ መብራት
የሚበራ ፡ በሰማያት
ነው ፡ አምላክ ፡ ፀባዖት ።

በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ የደረሰ ፡ ጭፍራ
ከብፁዓን ፡ ምዕመናን ፡ ይታደላል ፡ ደስታ
አሁን ፡ ነፍሤ ፡ ደስ ፡ ይልሻል
ያ ፡ ፍስሓ ፡ ይቆይሻል
ከአምላክ ፡ ፀባዖት ።

በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ ሥቃይና ፡ እንባዎች
ጥፋትም ፡ ሞትም ፡ በዚያ ፡ አይገኝም ፡ ለሰዎች
ይሰጣል ፡ ደስታ ፣ ሕይወትም
ይታደላል ፡ ሰላም ፣ ክብርም
ከአምላክ ፡ ፀባዖት ።

በሰማያት ፡ በሰማያት ፡ ብፅዕና ፡ የመላ
ሰዎች ፡ ያልቀመሱት ፡ ደስታ ፡ ይሰጠናል ፡ ጌታ
መዋቲ ፡ ልብ ፡ ያላሰበው
ሥጋዊ ፡ ድምፅ ፡ ያልዘመረው
ኦ! አምላክ ፡ ፀባዖት ።

ኦ! ዓብ ፣ ኦ! ወልድ ፣ ኦ! መንፈስም
ልወድስህ ፡ እርዳኝ
በሰማያዊ ፡ ቤትህም ፡ በምሕረትህ ፡ አግባኝ
አሁን ፡ በዕምነት ፡ ጠብቀኝ
አንድ ፡ ቀንም ፡ ዘውድ ፡ አቀብለኝ
ኦ! አምላክ ፡ ፀባዖት ።