ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን (Berhan Ayehu Gieta Yemesgen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ብርሃን ፡ አየሁ (፪x)
ጨለማው ፡ ጠፍቷል (፪x)
ተደስቻለሁ ፡ ሀዘኔም ፡ ርቋል
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

ብርሃን ፡ አየሁ (፪x)
በአንድ ፡ ሌሊት (፪x)
ብሩህ ፡ ነበር ፡ የማያቋርጥ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

ጭጋግ ፡ ነበር (፪x)
ብርሃን ፡ የነሳኝ (፪x)
አሁን ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ፈልጐ ፡ አገኘኝ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

መንገዱ ፡ የት ፡ ነው (፪x)
በእሣት ፡ ውስጥ (፪x)
ግን ፡ በኢየሱስ ፡ ደም ፡ መንፃት ፡ አገኘሁ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

ፍቅሩ ፡ ገዛኝ (፪x)
ብርሃኑም ፡ ሳበኝ (፪x)
ደስታን ፡ የሚሰጥ ፡ የሚያነጻኝ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

የሰላም ፡ ልዑል (፪X)
ብሩኅና ፡ ውብ (፪X)
ክርስቶስ ፡ ለእኔ ፡ ጓደኛ ፡ ሆነኝ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

የፍቅር ፡ ንጉሥ (፪x)
የንጋት ፡ ኮከብ (፪x)
መልካሙን ፡ ኢየሱስ ፡ ጌታ ፡ ክርስቶስን
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን

በኃጢአቴ (፪x)
ጨለማ ፡ ውጦኝ (፪x)
ጌታን ፡ አግኝቼ ፡ ተለወጥኩኝ
ብርሃን ፡ አየሁ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን