በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን (Berget Gieta Kegna Gar Bayhon)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን
እርሱ ፡ ባይዋጋልን
የጠላታችን ፡ ሠልፍ ፡ አይሎ
ከምድር ፡ ላይ ፡ በጠፋን
ስለዚህ ፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ስለ ፡ ሁሉም ፡ ነገር

ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን

የእሣት ፡ ሠረገላ ፡ ብዙ ፡ ሠልፍ ፡ ከቦናል
ከእኛ ፡ ጋራ ፡ ያለው ፡ ከሁሉም ፡ ይበልጣል
መለከትን ፡ ንፉ ፡ ጠላት ፡ ይታወራል
ብቻ ፡ ዕምነት ፡ ይኑረን ፡ ኢየሱስ ፡ ያሸንፋል

አዝ፦ በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን
እርሱ ፡ ባይዋጋልን
የጠላታችን ፡ ሠልፍ ፡ አይሎ
ከምድር ፡ ላይ ፡ በጠፋን
ስለዚህ ፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ስለ ፡ ሁሉም ፡ ነገር
ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን

በብዙም ፡ በጥቂት ፡ ማዳን ፡ ላይሳነው
ኤረ ፡ ለመሆን ፡ የሚነካን ፡ ማን ፡ ነው?
ቀድሞስ ፡ በባዕድ ፡ ግዛት ፡ መቆየት ፡ መች ፡ አሻን?
ይህስ ፡ ባይሆን ፡ ወንዙን ፡ ስለምን ፡ ተሻገርን?

አዝ፦ በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን
እርሱ ፡ ባይዋጋልን
የጠላታችን ፡ ሠልፍ ፡ አይሎ
ከምድር ፡ ላይ ፡ በጠፋን
ስለዚህ ፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ስለ ፡ ሁሉም ፡ ነገር
ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን

አለችን ፡ ውብ ፡ አገር ፡ ኗሪ ፡ ከተማ
በውስጧ ፡ የዕሮሮ ፡ ድምፅ ፡ የማይሰማ
እንጋደላለን ፡ እስክንጨብጣት
አምላክ ፡ ይረዳናል ፡ በምንደክምበት

አዝ፦ በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን
እርሱ ፡ ባይዋጋልን
የጠላታችን ፡ ሠልፍ ፡ አይሎ
ከምድር ፡ ላይ ፡ በጠፋን
ስለዚህ ፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ስለ ፡ ሁሉም ፡ ነገር
ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን

የአማሌቅ ፡ ተቃውሞ ፡ የፈርዖን ፡ ሠልፉ
በሠራዊት ፡ ጌታ ፡ እንድናይ ፡ ሲረግፉ
ድምፃችንን ፡ እናንሳ ፡ መለከትን ፡ ንፉ
የዕምነትን ፡ ጥሩር ፡ በራሣችሁ ፡ ድፉ

አዝ፦ በዕርግጥ ፡ ጌታ ፡ ከእኛ ፡ ጋር ፡ ባይሆን
እርሱ ፡ ባይዋጋልን
የጠላታችን ፡ ሠልፍ ፡ አይሎ
ከምድር ፡ ላይ ፡ በጠፋን
ስለዚህ ፡ ስለዚህ
እግዚአብሔር ፡ ይመስገን
ስለ ፡ ሁሉም ፡ ነገር
ለሥሙ ፡ ክብር ፡ ይሁን