ብርሃን ፡ በሌት ፡ እንደሚዘልቅ (Berehan Beliet Endemizelq)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ብርሃን ፡ በሌት ፡ እንደሚዘልቅ
የጌታ ፡ ቃል ፡ ይሰፋል
የዓለም ፡ ዘመንም ፡ ሲያልቅ
ዙፋኑ ፡ ይጋረዳል
ሥሙን ፡ በእምነት ፡ ሲጠሩ
ለመስቀሉ ፡ ይሰግዳሉ
የምድር ፡ ሕዝቦች ፡ ሁሉ

ሕፃናት ፡ ያቀርቡለታል
በሞት ፡ ጽላም ፡ ብርሃን ፡ ነው
በጭንቅም ፡ ለእርሱ ፡ ይጮኻል
በደስታ ፡ ቀን ፡ የረሳው
በመከራ ፡ በሐዘንም
ኃይል ፡ አጥቶ ፡ ለሚደክም
ሌላ ፡ ረድኤቴ ፡ አይገኝም

በሞት ፡ በሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ሁን
ወትሮ ፡ በአጠገባችን
ላክልን ፡ ቅዱስ ፡ መንፈሱን
በቆሰለ ፡ ልባችን
ኃይልን ፡ ስጠን ፡ በድካም
ሞትም ፡ ሲደርሰን ፡ በሰላም
አድነን ፡ ከዚህ ፡ ዓለም