From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
በራሴ ፡ አልመካም ፡ ጉድለቴ ፡ ብዙ ፡ ነው (፪x)
ሰው ፡ ከራሱ ፡ የሆነ ፡ ምን ፡ በጐነት ፡ አለው (፪x)
መንፈስ ፡ ግን ፡ ሲመጣ ፡ በኃይሉ ፡ ሲያግዘኝ
ጠላቴን ፡ እረታለሁ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ ብርቱ ፡ ነኝ (፪x)
አዝ፦ ከድካሜ ፡ በቀር ፡ ስለራሴ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው
ማን ፡ መንፈስህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
ጌታ ፡ ከደካማው ፡ ከትል ፡ ጋር ፡ ይቆማል (፪x)
ታላቁን ፡ ተራራ ፡ በፊቱ ፡ ይንዳል (፪x)
ያንተ ፡ መንፈስ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እንዳለ ፡ ሲሰማኝ
ማንነቴን ፡ ረሳሁ ፡ ኩራት ፡ ኩራት ፡ አለኝ (፪x)
አዝ፦ ከድካሜ ፡ በቀር ፡ ስለራሴ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው
ማን ፡ መንፈስህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
ማን ፡ መስዬሃለሁ ፡ በፊቴ ፡ የፎከርከው (፪x)
ጐልያድ ፡ ግዙፍ ፡ ሰው ፡ ግን ፡ ባዶ ፡ ቀፎ ፡ ነህ (፪x)
ምንም ፡ ታናሽ ፡ ብመስል ፡ ላልተገረዘ ፡ ዐይንህ
ወንጭፌ ፡ አይደለም ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የጣለህ (፪x)
አዝ፦ ከድካሜ ፡ በቀር ፡ ስለራሴ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው
ማን ፡ መንፈስህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
ደካማ ፡ መሆኔን ፡ ምንም ፡ ውስጤ ፡ ቢያውቀው (፪x)
እመካበታለሁ ፡ ድካሜ ፡ ኃይሌ ፡ ነው (፪x)
እኔ ፡ ልስማማ ፡ እንጂ ፡ ከመንፈሱ ፡ ጋራ
ከባሕር ፡ ይወድቃል ፡ ተነድሎ ፡ ተራራው (፪x)
አዝ፦ ከድካሜ ፡ በቀር ፡ ስለራሴ ፡ የለኝም ፡ የማውቀው
ማን ፡ መንፈስህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ፡ እጅግ ፡ ኃይለኛ ፡ ነው
|