በእምነት ፡ እኖራለሁ (Bemnet Enoralehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

1. ከምድር ፡ በላይ ፡ ቢሆን ፡ ከሰማይም ፡ በታች
መግባት ፡ መውጣታችንን ፡ ዘወትር ፡ ተመልካች
እንደ ፡ ኢየሱስ ፡ ያለ ፡ ማንን ፡ አገኛችሁ
የሕይወት ፡ ዋስትና ፡ ቤዛ ፡ የሚሆናችሁ

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፡ ጽኑ ፡ እምባ ፡ ተጠልዬዋለሁ
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ

2. ለነገ ፡ አያስጨንቀኝም ፡ ጭጋግ ፡ ቢሸፍነው
ውይኑም ፡ ቢጠወልግ ፡ ሐሩሩ ፡ ቢያሰጋው
ለእግሬ ፡ መብራት ፡ ነው ፡ ቃሉ ፡ በእጄ ፡ ያለው
የተፈጥሮ ፡ አዛዥ ፡ ኢየሱስ ፡ ሕያው ፡ ነው

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፡ ጽኑ ፡ እምባ ፡ ተጠልዬዋለሁ
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ

3. ፈቃዱ ፡ ሲሞላ ፡ ጌታዬ ፡ ከብሮ ፡ ሳይ
ምድር ፡ እልል ፡ ስትል ፡ ሲያጨበጭብ ፡ ሰማይ
መጠለያዬ ፡ ልብሴ ፡ እንጀራዬ ፡ ያ ፡ ነው
ነፍሴ ፡ ትጠግባለች ፡ በክብር ፡ በግርማው

አዝ፦ በእምነት ፡ እኖራለሁ ፡ ጌታዬን ፡ አውቃለሁ
የእኔን ፡ ጽኑ ፡ እምባ ፡ ተጠልዬዋለሁ
ወጀቡን ፡ ሳልፈራ ፡ ታግዬ ፡ እረታለሁ
የክብር ፡ ሽልማቴን ፡ ከእጁ ፡ እረከባለሁ