From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
ቀናትም ፡ ያልፍና ፡ ዘመን ፡ ተፈጽሞ
የክርስቲያን ፡ ፈተና ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አክትሞ
በጥፋት ፡ ዓለም ፡ ውስጥ ፡ መኖር ፡ ያበቃና
የዐይናችንን ፡ እንባ ፡ ጌታ ፡ ይጠርግና
አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአስራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና
ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያ ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና
መች ፡ ይላል ፡ ተመስገን ፡ ጊዜው ፡ ይደርስና
ከልቡ ፡ አልቅሶ ፡ ለጌታው ፡ ይነግርና
ምኞቱም ፡ ጥረቱም ፡ መቼ ፡ ይሳካና
ጌታም ፡ ሲል ፡ ይሰማል ፡ ልጄ ፡ ሆይ ፡ ተጽናና
አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአስራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና
ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያ ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና
አዕላፋት ፡ ጻድቃን ፡ ከምድር ፡ እንሄድና
ነጭ ፡ ልብሳችንን ፡ ለብሰን ፡ ዙፋን ፡ እንከብና
ኪሩቤል ፡ ላይ ፡ ላለው ፡ ለበጉ ፡ እንሰግድና
መቼ ፡ እንዘምር ፡ ይሆን ፡ ለኤኢየሱስ ፡ ምሥጋና
አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአስራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና
ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያ ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና
የምድር ፡ መጻተኛ ፡ ልብህ ፡ የተሰቀለ
ስማዕትን ፡ ለማየት ፡ ተስፋህ ፡ ያልጐደለ
መቼ ፡ ቀን ፡ ሞልቶልህ ፡ ጽዮን ፡ ትደርስና
ጌታን ፡ በዐይንህ ፡ አይተህ ፡ ልብህ ፡ ይረካና
አዝ፦ በመዝሙር ፡ ውዳሴ ፡ በቅኔ ፡ ምሥጋና
በአስራ ፡ ሁለት ፡ አውታር ፡ በታላቅ ፡ በገና
ምሥጋና ፡ እንልና
ዕልልታው ፡ ሽብሸባው ፡ በዚያ ፡ ይደምቅና
መቼ ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ ፡ ጌታም ፡ ይከብርና ፡ ምሥጋና
|