በመስቀል ፡ ሞተ ፡ መድኃኒቴ (Bemesqel Mote Medhanitie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በመስቀል ፡ ሞተ ፡ መድኃኒቴ
ሊያድነኝ ፡ ብሎ ፡ ከጥፋቴ
ሊመልሰኝም ፡ ከኃጢአቴ
ክብር ፡ ለስሙ

አዝ፦ ክብር ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ለስሙ
ነጻ ፡ ስላወጣኝ ፡ በደሙ
ክብር ፡ ለስሙ

በመስቀሉ ፡ ከኃጢአት ፡ ዳንሁኝ
አምላክም ፡ ልጁን ፡ ለወጠልኝ
ከኃጢአት ፡ አርነት ፡ ሊያወጣኝ
ክብር ፡ ለስሙ

አዝ፦ ክብር ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ለስሙ
ነጻ ፡ ስላወጣኝ ፡ በደሙ
ክብር ፡ ለስሙ

ኦ! ቡሩክ ፡ ምንጭ ፡ ከኃጢአት ፡ ያዳነኝ
ያ ፡ ምንጭም ፡ አንጽቶ ፡ አጠበኝ
ያማልደኝ ፡ ዘንድም ፡ ተስፋ ፡ አለኝ
ክብር ፡ ለስሙ

አዝ፦ ክብር ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ለስሙ
ነጻ ፡ ስላወጣኝ ፡ በደሙ
ክብር ፡ ለስሙ

ያ ፡ ምንጭም ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው!
ለኃጢአታችን ፡ ሲል ፡ የሞተው
በሦስተኛም ፡ ቀን ፡ የተነሣው
ክብር ፡ ለስሙ

አዝ፦ ክብር ፡ ለስሙ
ክብር ፡ ለስሙ
ነጻ ፡ ስላወጣኝ ፡ በደሙ
ክብር ፡ ለስሙ