በምሥጋና ፡ ዝመቱ (Bemesgana Zemetu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ዝመቱ
በምሥጋና ፡ ዛሬ
በምሥጋና ፡ ተዋጉ
በዝማሬ!

እሥራኤል ፡ ለውጊያ ፡ ጦርነት ፡ ሲወጣ
ጠላትም ፡ በትምክህት ፡ ሊፎክር ፡ ሲመጣ
ይሁዳም ፡ አምላኩን ፡ ማመስገን ፡ ሲጀምር
እግዚአብሔር ፡ አስነሣ ፡ ድብቅ ፡ ጦር

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ዝመቱ
በምሥጋና ፡ ዛሬ
በምሥጋና ፡ ተዋጉ
በዝማሬ!

ምሕረቱን ፡ ኪዳኑን ፡ ተስፋውን ፡ ዘምሩ
ማዳን ፡ ተዓምራቱን ፡ ቸርነቱን ፡ አውሩ
ጌታችን ፡ በቁጣ ፡ በበቀል ፡ ይወርዳል
ምርኮን ፡ በምርኮ ፡ ላይ ፡ ያበዛል

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ዝመቱ
በምሥጋና ፡ ዛሬ
በምሥጋና ፡ ተዋጉ
በዝማሬ!

ሠልፉ ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ያሸንፋል! በሉ
ከበሮ ፡ ይዛችሁ ፡ በፊቱ ፡ ዝለሉ
ጠላት ፡ በዚያች ፡ ጊዜ ፡ ጉልበቱ ፡ ይቀልጣል
ክብሩም ፡ ለአምላካችን ፡ ይሆናል !