በምሥጋና ፡ ሆ ፡ ድል ፡ ይገኛልና (Bemesgana Ho Del Yegegnalena)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሆ!
በምሥጋና ፡ ድል ፡ ይገኛልና (፪x)

ሸለቆ ፡ አሽቆልቁለው ፡ ሲያለቅሱ
ሰዎች ፡ ለምሥጋና ፡ ቢነሱ
በሐዘኑ ፡ ፈንታ ፡ ደስታ
በለቅሶውም ፡ ምትክ ፡ ዕልልታ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሆ!
በምሥጋና ፡ ድል ፡ ይገኛልና (፪x)

አይዞህ ፡ የሚል ፡ ቃላት ፡ ሲጠፋ
ጭው ፡ ካለው ፡ በረሃ ፡ ሲደፋ
ውኃ ጥም ፡ ሲተካ ፡ በእርካታ
ምሥጋና ፡ ሲታጀብ ፡ በሆታ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሆ!
በምሥጋና ፡ ድል ፡ ይገኛልና (፪x)

ሰማያት ፡ እንደ ፡ ናስ ፡ ሊዘጉ
በምሥጋና ፡ ሕይወት ፡ ቢጠጉ
ያንዣበበው ፡ ጥላ ፡ ሲገፈፍ
አመስግኖ ፡ በአምላክ ፡ መደገፍ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሆ!
በምሥጋና ፡ ድል ፡ ይገኛልና (፪x)

ብቅ ፡ ሲል ፡ ካለበት ፡ ሸለቆ
ፊቱ ፡ ፈገግ ፡ ሲልም ፡ ስቆ
የጮኽበት ፡ ጥሪ ፡ ተሰምቶ
በምሥጋና ፡ ሆ ፡ ሲል ፡ እረክቶ

አዝ፦ በምሥጋና ፡ ሆ!
በምሥጋና ፡ ድል ፡ ይገኛልና (፪x)