በመቃብር ፡ ተኛ ፡ የዓለም ፡ መድኅን (Bemeqaber Tegna YeAlem Medhen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በመቃብር ፡ ተኛ ፡ የዓለም ፡ መድኅን
ከዚያም ፡ ወጣ ፡ ለእኛ ፡ መድኃኒታችን

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ተነሣ
ድል ፡ ነሥቶልን ፡ በጠላቱ ፡ ላይ
ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶ ፡ ለእኛ ፡ ተነሣ
ለዘለዓለም ፡ ሊነግሥልን ፡ በሰማይ
ተነሣ ፡ ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶልን ፡ ተነሣ

በከንቱ ፡ ጠበቁት ፡ የእርሱን ፡ መቃብር
በከንቱም ፡ አተሙት ፡ የሕንጻን ፡ በር

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ተነሣ
ድል ፡ ነሥቶልን ፡ በጠላቱ ፡ ላይ
ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶ ፡ ለእኛ ፡ ተነሣ
ለዘለዓለም ፡ ሊነግሥልን ፡ በሰማይ
ተነሣ ፡ ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶልን ፡ ተነሣ

ሞትን ፡ አሸነፈ ፡ የዓለም ፡ መድኅን
ሕንጻን ፡ ፈነቀለ ፡ መድኃኒታችን

አዝ፦ ከመቃብር ፡ ተነሣ
ድል ፡ ነሥቶልን ፡ በጠላቱ ፡ ላይ
ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶ ፡ ለእኛ ፡ ተነሣ
ለዘለዓለም ፡ ሊነግሥልን ፡ በሰማይ
ተነሣ ፡ ተነሣ ፡ ድል ፡ ነሥቶልን ፡ ተነሣ