በመላ ፡ ዓለም ፡ ጭንቀት ፡ ይበዛል (Bemela Alem Chenqet Yebezal)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በመላ ፡ ዓለም ፡ ጭንቀት ፡ ይበዛል
በሽታና ፡ ድካም ፡ መልቶበታል
ጦር ፡ መረረነ ፡ ኃጢአት ፡ ይገፋል
ፈተና ፡ ቀርቦ ፡ ይሸምቃል

በዬት ፡ ይገኛል ፣ ሕይወት ፡ ለሞቱ
መድኅን ፡ ለሕመሙም ፡ ኃይል ፡ ለዛሉ
ምግብ ፡ ለተራቡ ፡ ደስታ ፡ ለባቡ
ድፍረት ፡ ለፈሩ ፡ ከደከሙ

ወንጌልን ፡ ሥሙ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲጠራ
ሁሉ ፡ ወደኔ ፡ አሁን ፡ ይምጣ
ራብተኛ ፡ ይጥገብ ፡ ጥማተኛ ፡ ይርካ
ሕዝቡ ፡ ይቀበል ፡ ቅዱስ ፡ ደስታ

እርሱ ፡ ሞተልን ፡ አስታረቀነ
አፍስሶ ፡ ደሙን ፡ ሊዋጀነ
ጽድቅን ፡ አመጣ ፡ ሰላም ፡ አስገኘ
ፀጋን ፡ ይሰጣል ፡ ለታመነ

ጤናና ፡ ሕይወት ፡ የሚፈስበት
ያደርገናል ፡ አዲስ ፡ ፍጥረት
ያሳድረናል ፡ ፍቅር ፡ ቸርነት
ኢየሱስ ፡ አግባልን ፡ ጽኑ ፡ ዕምነት