በመከራ ፡ ጊዜ (Bemekera Gizie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በመከራ ፡ ጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ አስበኝ
በክህደቴም ፡ ምክንያት ፡ እንዳትለየኝ
ዕምነቴ ፡ መድከሙ ፡ በመልኬ ፡ ሲታይ
አትተወኝ ፡ ጌታ ፡ ከአንተ ፡ እንዳልለይ

በማይጠቅም ፡ ደስታ ፡ ዓለም ፡ ያታልላል
በተንኮልም ፡ ወጥመድ ፡ ሰውን ፡ ያጠምዳል
አስታውሰኝ ፡ ያን ፡ ጊዜ ፡ ጌቴሰማኔን
ደግሞም ፡ ቀራንዮን ፡ የእሾህ ፡ አክሊልህን

ሐዘንን ፡ ችግርን ፡ በምሕረት ፡ ብትሰድ
ሕመም ፡ ቢደርስብኝ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ ስሄድ
አደራ ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ እጅህ ፡ ይታየኝ
ችግሬን ፡ ስነግርህ ፡ አምላክ ፡ ደግፈኝ