በልብህ ፡ ያለውን ፡ ትካዜህን ፡ ጣል (Belebeh Yalewen Tekaziehen Tal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በልብህ ፡ ያለውን ፡ ትካዜህን ፡ ጣል
በተስፋም ፡ ተቀበል ፡ የኢየሱስን ፡ ቃል
በጣም ፡ ብትጨነቅ ፡ በዚህ ፡ በመሬት
ከላይ ፡ ተጠባበቅ ፡ የጌታን ፡ ረድዔት

ድካምህን ፡ ሁሉ ፡ ለኢየሱስ ፡ ንገር
ያዳምጥሃል ፡ አትመረር
ሃዘንህም ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ እስኪሻር
አምላክን ፡ በዕምነት ፡ መጠበቅ ፡ ተማር

ከአንተ ፡ ይልቅ ፡ የተቸገሩትም
እንዳሉ ፡ ለማሰብ ፡ ይገባሃልም
ለርሳቸውም ፡ ረድዔት ፡ ልትሰጥ ፡ ብትጥር
በዕርግጥ ፡ ይቀላል ፡ የራስህ ፡ ችግር