From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)
ጠላት ፡ ሊያጠቃን ፡ በብርቱ ፡ ሲሮጥ
ኤርትራ ፡ ሞልቶ ፡ ልባችን ፡ ሲቀልጥ
የእኛማ ፡ ነገር ፡ አበቃ ፡ ስንል
ወርዶ ፡ ደረሰ ፡ አምላክ ፡ አዳነን
አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)
እጅግ ፡ ሲመኩ ፡ በፈረሳቸው
አላመለጡም ፡ ደረስንባቸው
ብለው ፡ በትዕቢት ፡ እየፎከሩ
ባሕር ፡ ዋጣቸው ፡ ሳይወጡ ፡ ቀሩ
አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)
ጠላታችንን ፡ ከባሕር ፡ ጥሎ
ያስጨነቀንን ፡ ሁሉ ፡ አስወግዶ
ዛሬ ፡ ዝማሬ ፡ ጉልበት ፡ ሆነልን
ያ ፡ ሁሉ ፡ አልፎ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርን
አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)
ከዛ ፡ ባርነት ፡ ነጻ ፡ ያወጣን
ቀንበራችንን ፡ የሰበረልን
በድንቅ ፡ በተዓምር ፡ በድል ፡ የመራን
እግዚአብሔር ፡ ነው ፡ ለዚህ ፡ ያበቃን
አዝ፦ በክብር ፡ ከፍ ፡ ብሎአልና
እንዘምር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ምሥጋና (፪x)
|