በኃጢአቴ ፡ ተፀጽቼ (Behatiatie Tetsetsechie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በኀጢአቴ ፡ ተፀጽቼ
መጣሁ ፡ ጌታ ፡ ተቀበለኝ
ጸጋህ ፡ ተለይቶኝ ፡ ጭው ፡ ባለው ፡ በረሃ
በሐዘን ፡ ውስጥ ፡ እጓዛለሁ

የጸሎት ፡ ጊዜዬ ፡ ትዝ ፡ ሲለኝ
መስቀልህ ፡ ስር ፡ ተንበርክኬ
የነበረኝ ፡ ደስታ ፡ ዘለዓለማዊው
አሁን ፡ ጠፍቶብኝ ፡ አለቅሳለሁ

ጌታ ፡ ኢየሱሴ ፡ ሌላው ፡ ይቅርብኝ
በየቀኑ ፡ መስቀልህን ፡ ልይ
ብሞትም ፡ እንኳን ፡ ዝግጁ ፡ ነኝ
ቅዱስ ፡ ደምህ ፡ እንጽቶኛል

ወደ ፡ ኋላዬ ፡ ላልመለስ
ቆርጫለሁ ፡ እጄን ፡ ያዘኝ
ነፍሴን ፡ አደራ ፡ ሰጥቼሃለሁ
ከልጆችህ ፡ አንዱ ፡ አርገኝ