በጊዜውም ፡ አለጊዜውም (Begiziewem Alegiziewem)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ዘወትሮ ፡ በሁሉም ፡ ስፍራ
አንተን ፡ ልምሰል ፡ አንተን ፡ ልፍራ
ከዓለም ፡ አድርገኝ ፡ ልዩ
በእኔም ፡ ሕይወት ፡ አንተን ፡ ይዩ
ሥጋዬን ፡ ለዓለም ፡ ሰቅዬ
ልጓዝ ፡ አንተን ፡ ተከትዬ

አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
በስምህ ፡ ጸንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ
እሩጫዬን ፡ ፈጸሜ
ስለዚህ ፡ ፍቃድህ ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ

በድካም ፡ ሕይወቴ ፡ ላልቶ
አካሄዴም ፡ ተበላሽቶ
ቅዱስ ፡ ስምህ ፡ እንዳይሰደብ
አደራ ፡ ልጅህን ፡ አስብ
እስክትመጣልኝ ፡ በክብር
አንተን ፡ አስከብሬ ፡ ልኑር

አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
በስምህ ፡ ጸንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ
እሩጫዬን ፡ ፈጸሜ
ስለዚህ ፡ ፍቃድህ ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ

በከፍታም ፡ በዝቅታም
በሐዘንም ፡ በደስታም
ሳልደናገር ፡ በእርጋታ
በፈተናም ፡ ሳልረታ
በሥጋት ፡ ጸንቼ ፡ በምድር
ፊትህን ፡ ልየው ፡ በክብር

አዝ፦ በጊዜውም ፡ አለጊዜውም
በስምህ ፡ ጸንቼ ፡ ቆሜ
ፊትህን ፡ ለማየት ፡ እጓጓለሁ
እሩጫዬን ፡ ፈጸሜ
ስለዚህ ፡ ፍቃድህ ፡ ይሁንልኝ ፡ ውድ ፡ አባቴ
በሰላም ፡ በጤና ፡ አድርሰኝ ፡ ከቤቴ