በደመና ፡ ይመለሣል (Bedemena Yemelesal)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሣል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)

አባት ፡ እንደሌው ፡ አልተዋችሁም
ሥፍራ ፡ ላዘጋጅ ፡ ነው ፡ እንድወስዳችሁ
ልባችሁ ፡ አይፍራ ፡ በእኔ ፡ እመኑ
ቶሎ ፡ እመለሣለሁ ፡ ልወስዳችሁ

አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሣል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)

ድንኳን ፡ መኖሪያችን ፡ ይህ ፡ ቤታችን
ቢፈርስ ፡ ተስፋ ፡ ቢያጣ ፡ ኑሯችን
በእጅ ፡ ያልተሠራ ፡ ቤት ፡ ተዘጋጅቷል
ተስፋችን ፡ ላይኛይቱ ፡ ጽዮን ፡ ናት

አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሣል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)

የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሮ ፡ ያበቃል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሊወስደን ፡ ይመጣል
ብርሃን ፡ በሞላበት ፡ ቅድስት ፡ ሃገር
ጊዜው ፡ ተዳርሷል ፡ ልንሄድ ፡ ልንዘምር

አዝ፦ በደመና ፡ ይመለሣል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል (፪x)