በደመና ፡ ይመለሳል (Bedemena Yemelesal)
From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል
አባት ፡ እንደሌለው ፡ አልተዋችሁም
ስፍራ ፡ ላዘጋጅ ፡ እንድወስዳችሁ
ልባችሁ ፡ አይፍራ ፡ በእኔ ፡ እመኑ
ቶሎ ፡ እመለሳለሁ ፡ ልወስዳችሁ
በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል
ድንኳን ፡ መኖሪያችን ፡ ቤታችን
ቢፈርስ ፡ ተስፋ ፡ ቢያጣ ፡ ኑሯችን
በእጅ ፡ ያልተሰራች ፡ ጌታ ፡ ያዘጋጃት
ተስፋችን ፡ ላይኛይቱ ፡ ጽዮን ፡ ናት
በደመና ፡ ይመለሳል
በሚያስደንቅ ፡ ክብር ፡ ይገለጣል
ልጆቹን ፡ ፍለጋ ፡ ይመጣል
የዚህ ፡ ዓለም ፡ ኑሯችን ፡ ያበቃል
ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ሊወስደን ፡ ይመጣል
ብርሃን ፡ በሞላባት ፡ ቅድስት ፡ ሃገር
ጊዜው ፡ ደርሷል ፡ ልንሄድ ፡ እንድንዘምር
|