በብፁዓን ፡ መኖሪያ ፡ ርስታችን ፡ አለነ (Bebitsuan Menoriya Ristachin Alene)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በብፁዓን ፡ መኖሪያ
ርስታችን ፡ አለነ
በኢየሱስ ፡ ደምም ፡ ወዲያ
መግባት ፡ ተሰጠነ ።
መስቀሉን ፡ ተሸክመን
መከራም ፡ ታግሠን
አክሊሉን ፡ እንድንጭን
እንጓዝ ፡ ወደ ፡ ሰማይ ።

ከሞትም ፡ ባሕር ፡ ወዲያ
ነፋሱ ፡ ፀጥ ፡ ይላል
የአሁኑ ፡ ችግር ፡ በዚያ
አልቆ ፡ ይለቀናል ።
መስቀሉን ፡ ተሸክመን
መከራም ፡ ታግሠን
አክሊሉን ፡ እንድንጭን
እንጓዝ ፡ ወደ ፡ ሰማይ ።

በኢየሱስ ፡ የተሠራው ፡ ቤት
ይከፈትልናል
የመረጣቸውም ፡ ከመሬት
ድነው ፡ ይቆዩናል ።
መስቀሉን ፡ ተሸክመን
መከራም ፡ ታግሠን
አክሊሉን ፡ እንድንጭን
እንጓዝ ፡ ወደ ፡ ሰማይ ።

ከምድሩ ፡ ከንቱነትም
ልባችን ፡ ወደ ፡ ላይ
ይናፍቃል ፣ ይመኛልም
ደስታችን ፡ ነው ፡ በላይ ።
መስቀሉን ፡ ተሸክመን
መከራም ፡ ታግሠን
አክሊሉን ፡ እንድንጭን
እንጓዝ ፡ ወደ ፡ ሰማይ ።