በቤተልሔም ፡ በረት (Bebethlehem Beret)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በቤተልሔም ፡ በረት
ግሩም ፡ ነገር ፡ አይተናል
የአምላካችን ፡ ምሕረት
አሁን ፡ ጐብኝቶናል
በዳዊት ፡ አገር ፡ መድህን
ዛሬ ፡ ተወለደልን
እርሱም ፡ ክርስቶስ ፡ ጌታ

በበረት ፡ ውስጥ ፡ የተኛ
ህፃን ፡ ጌታችን ፡ ነው
ተወለደ ፡ እንደ ፡ እኛ
እንደ ፡ አብ ፡ ግን ፡ አምላክ ፡ ነው
ለእርሱም ፡ ይሰግዳሉ
የምድር ፡ አሕዛብ ፡ ሁሉ
መድኃኒታችን ፡ ነው

እኛም ፡ እንደ ፡ መልአኩ
አሁን ፡ እናመስግን
አንድ ፡ ልጁን ፡ በመላኩ
አምላክ ፡ ሁሉን ፡ ሰጠን
ለአምላካችን ፡ ክብር
ሰላም ፡ በዚህ ፡ በምድር
ለሰውም ፡ በጐ ፡ ፈቃድ