በዓለሙ ፡ እንደ ፡ ቤቴ ፡ የለም (Bealemu Endebiete Yelem)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በዓለሙ ፡ እንደ ፡ ቤቴ
የለም ፡ የከበረ ፡ ለእኔ
የሚወደው ፡ ልቤ
ጐጆ ፡ ሆኖ ፡ ምንም ፡ እንኳ
ጌጥና ፡ ውበት ፡ ቢያጣ
ከንጉሥ ፡ አዳራሽ ፡ ቤቴ
ክቡር ፡ ሆነ ፡ ለእኔ

የወደዱኝ ፡ ወላጆቼ
ከታናሽነቴ ፡ ጊዜ
ይዘው ፡ ጣሩ ፡ ለእኔ
ሥራቸው ፡ ቤትን ፡ አቆመ
ፍቅራቸውም ፡ ያን ፡ አሞቀ
ፍቅር ፡ ሰላም ፡ የኖረበት
አልረሳም ፡ ያንን ፡ ቤት

ቤቴ ፡ በሁሉ ፡ መከራ
ይሆነኛል ፡ መጠጊያ
በችጋርም ፡ አምባ
የሌላ ፡ ቤት ፡ ሲዘጋብኝ
አንድ ፡ ቤት ፡ ተከፍቶ ፡ ሊቆየኝ
እንደ ፡ እናቴ ፡ ልብ ፡ ቤትም
በዓለም ፡ አይገኝም

በዚያ ፡ ቁስል ፡ ይጠጋል
እንባ ፡ ከዓይን ፡ ይታበሳል
ልቤ ፡ ይጸናናል
ትዕግሥት ፡ ለስንፍናዬ
ሥርየት ፡ ለሁሉ ፡ በደሌ
በጭንቀት ፡ ይገኛል ፡ ረድዔት
በወላጆቼ ፡ ቤት

ያ ፡ ቤት ፡ ግን ፡ ወድሞ ፡ ሊቀር
ወላጆች ፡ ለቀው ፡ ከምድር
ሲገቡ ፡ መቃብር
በአምላክ ፡ ቤት ፡ ግን ፡ ሳይለዩ
ልጆቹ ፡ ሊተባበሩ
ፍቅር ፡ ደስታ ፡ በመላበት
በሰማያዊ ፡ ቤት