በዓለም ፡ ፊት ፡ ራሱን ፡ ጥሎ (Bealem Fit Rasun Telo)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

እንደ ፡ ንፁሕ ፡ የማር ፡ ወለላ
እንደ ፡ ጥሩ ፡ የወይን ፡ ዘለላ
እንደ ፡ ክቡር ፡ የዕንቁ ፡ ፍካች
ፍቅሩ ፡ አይደለም ፡ ታካች

አዝ፦ በዓለም ፡ ፊት ፡ ራሱን ፡ ጥሎ
ዝቅ ፡ አድርጐ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ የተነዳው
የታረደው ፡ የቆሰለው ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ ፡ ነው

ተሯሩጬ ፡ በዓለም ፡ ታክቼ
ተራወጥኩ ፡ ብዙ ፡ ለፍቼ
ሰልችቶኝ ፡ ፊቴን ፡ ሳቀና
ፍቅር ፡ ይለኛል ፡ ና

አዝ፦ በዓለም ፡ ፊት ፡ ራሱን ፡ ጥሎ
ዝቅ ፡ አድርጐ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ የተነዳው
የታረደው ፡ የቆሰለው ፡ ፍቅር ፡ኢየሱስ፡ ነው

ወዴት ፡ ነህ ፡ ብሎ ፡ የሚፈልግ
እንባህን ፡ የሚጠራርግ
የሚራራልህ ፡ ሰው ፡ ከተመኘህ
ፍቅር ፡ ይኸውልህ

አዝ፦ በዓለም ፡ ፊት ፡ ራሱን ፡ ጥሎ
ዝቅ ፡ አድርጐ ፡ ወደ ፡ ሞት ፡ የተነዳው
የታረደው ፡ የቆሰለው ፡ ፍቅር ፡ ኢየሱስ፡ ነው