በአፋችሁ ፡ ከልባችሁ (Beafachehu Kelebachehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በአፋችሁ ፡ ከልባችሁ
ክርስቶስን ፡ አመስግኑ
ስለ ፡ እኛ ፡ ሞተ
ተኛ ፡ ሦስት ፡ ቀን ፡ በመቃብሩ
ከመቃብርም ፡ በክብር ፡ ተነሣ
ሃሌ ፡ ሉያ !

የእኛን ፡ ሥራ ፡ እርሱ ፡ ሠራ
ለእኛ ፡ ጽድቅ ፡ ይሰጠናል
ኃጢአታችን ፡ ችግራችን
አሁን ፡ ፍፁም ፡ ጠፍቶአል
በሞት ፡ ፈንታ ፡ ሕይወት ፡ ደስታ
ሰጠነ ፤ ሃሌ ፡ ሉያ !

ልንፈታ ፡ እርሱ ፡ መጣ
ያለም ፡ ቤዛ ፡ እርሱ ፡ ነው
አሁን ፡ ሰይጣን ፡ ኃይሉን ፡ አጣ
ኃይልም ፡ ሁሉ ፡ ለልጅ ፡ ነው
አሁን ፡ እኛን ፡ ኃጢአተኞች
አዳነን ፤ ሃሌ ፡ ሉያ !

እናንት ፡ ሁሉ ፡ በድምጽ ፡ ምሉ
አምላክን ፡ አመስግኑ
ለልጅ ፡ ደግሞ ፡ ክብርን ፡ ስጡ
ስለ ፡ ታላቅ ፡ ምሕረቱ
ለሚቀድስ ፡ መንፈስ ፡ ቅዱስ
ዘምሩ ፤ ሃሌ ፡ ሉያ !