በመድሃኔ ፡ ዓለሙ ፡ ላመኑት ፡ ሁሉ (BeMedihane Alemu Lamenut Hulu)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በመድሃኔ ፡ ዓለሙ ፡ ላመኑት ፡ ሁሉ
ዕለተ ፡ ፍርድ ፡ የዕልልታ ፡ ቀን ፡ ነው
በዕለተ ፡ ፍርድም ፡ ሰላም ፡ ያገኛሉ
መከራ ፡ ሁከትም ፡ የማይነካው
ትግል ፣ ድካም
ሆኖ ፡ ሰላም
ውርደቱን ፡ ክብረት ፡ ይከተለዋል

አልተዘጋጀሁም ፡ ሲል ፡ የሚፈራ
እንዳይደርስበት ፡ በድንገት ፡ ያ ፡ ቀን
ወደ ፡ መድኃኒቱ ፡ እርሱ ፡ ይመራ
በትሩፋቱም ፡ በቁስሉም ፡ ይመን
የክርስቶስ ፡ ደም
ሕማማቱም
የእኛ ፡ ሲሆን ፡ እንሙት ፡ በሰላም

ሞትና ፡ ፍርድ ፡ እስካሁን ፡ ቢያስፈራህ
የኢየሱስ ፡ ክርስቶስን ፡ ሞት ፡ አስበው
ከኃጥአትና ፡ ሞት ፡ ሊያጠራህ
እርሱ ፡ መዓትህን ፡ ተሸከመው
እንዳዳነን
ለሚያምን
ደስታ ፡ ይሰጣል ፡ የፍርድ ፡ መለከት

ኦ! ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ግለጥ ፡ ለልባችን
ምን ፡ እንደሆነ ፡ የአንተ ፡ ትሩፋት
አንተ ፡ ከሞትህ ፡ ስለ ፡ ኃጥአታችን
ዓለሙ ፡ ዳነ ፡ ከፍርድና ፡ ሞት
ዕምነት ፡ ስጠን ፣
በፍርድም ፡ ቀን
በቀኝ ፡ ከበጐችህ ፡ ጋር ፡ አድርገን