በኢየሱስ ፡ ፊት ፡ ይቆማሉ ፡ ታላቅ ፡ ወገን (BeEyesus Fit Yiqomalu Talaq Wogen)
From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
|
|
ሌሎች ፡ የድሮ ፡ መዝሙሮች (Other Classic Mezmur Lyrics)
|
|
በኢየሱስ ፡ ፊት ፡ ይቆማሉ
ታላቅ ፡ ወገን
ከሕዝቦች ፡ የተለቀሙ
አዕላፎች ፡ ቅዱሣን
ነጭ ፡ ልብስን ፡ ለብሰው ፡ ዘንባባን
በእህ ፡ ጨብጠው
ከፍ ፡ አድርገው ፡ ድምፃቸውን
ጮኹ ፡ እንዲህ ፡ ብለው
መድኃኒት ፡ በዙፋኑ ፡ ላይ
ለሚቀመጥ
ለአምላካችን ፡ በሰማይ
ምሥጋናን ፡ ልንሰጥ
መላዕክትም ፡ ቁመው ፡ በዚያ
ከሽማግሎች
ከአራት ፡ እንስሶች ፡ ዙሪያ
የሰማያት ፡ ጭፍሮች
በግምባራቸው ፡ ወደቁ
ሊሰግዱ
ለልዑል ፡ አምላክ ፡ ለበጉ
ስብሓት ፡ ይሁን ፡ ሲሉ
ግርማና ፣ ክብር ፣ ጥበብም
ለአንተ ፡ ይሁን
ምሥጋና ፣ ኃይልም ፣ ችሎትም
ይገባሃል ፤ አሜን ።
|