በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን (BeEden And Qen)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

ስንሰበሰብ ፡ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን
በሰማያዊ ው፡ አገር
በላይ ፡ መከራና ፡ ሃዘን ፡ ይጨረሳል
በሰማይ ፡ ዳርቻ ፡ ስንቆም

አዝ፦ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ (፪X)
መከራና ፡ ሃዘን ፡ ይጨረሳል
በሰማይ ፡ ዳርቻ ፡ አንድ ፡ ቀን

ስንሰበሰብ ፡ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን
ልንኖር ፡ ከጌታችን ፡ ጋራ
ጻድቃን ፡ ሁሉ ፡ በሰማይ ፡ ሲደርሱ
በዚያ ፡ ልናገኛቸው ፡ ነው

አዝ፦ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ (፪X)
መከራና ፡ ሃዘን ፡ ይጨረሳል
በሰማይ ፡ ዳርቻ ፡ አንድ ፡ ቀን

ስንሰበሰብ ፡ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን
ከነቢያትና ፡ ከቅዱሣን
ታናሽ ፡ ልጆች ፡ የሞቱ
በሃይማኖት ፡ ይቆማሉ
በዙፋኑ ፡ ፊት

አዝ፦ በኤደን ፡ አንድ ፡ ቀን ፡ (፪X)
መከራና ፡ ሃዘን ፡ ይጨረሳል
በሰማይ ፡ ዳርቻ ፡ አንድ ፡ ቀን