በአምላክ ፡ ተመርተን ፡ በቃሉ ፡ ብርሃን (BeAmlak Temerten Beqalu Berhan)

From WikiMezmur, the free amharic mezmur lyrics database.
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

በአምላክ ፡ ተመርተን ፡ በቃሉ ፡ ብርሃን
በልጁም ፡ ሲጸና ፣ የምሕረት ፡ ኪዳን
ያላየነው ፡ ዘመን ፡ ሲብት ፡ አንፍራ
ያ ፡ ቸር ፡ እረኛችን
ሲኖር ፡ በቅርባችን
ሲሄድ ፡ በፊታችን
ከምን ፡ እንፍራ?

ከጨለማ ፡ ዓለም ፣ ከምድር ፡ ሥቃይ
አንድ ፡ ጭፍራ ፡ ተነሣ ፡ ሊጓዝ ፡ ወደ ፡ ላይ
የጭፍራውም ፡ ገናነት ፡ ተሠውሯል
ግን ፡ አምላክ ፡ ሲቀድም
ሲከተል ፣ ሲከብም
ሲደግፍ ፣ ሲሸከም
ይጋርደዋል

ከንቱነቱን ፡ ዓለም ፡ ሲፈልግ ፡ ሲሻው
በርኩሰትም ፡ ብቻ ፡ ሲሆን ፡ ደስታው
ያን ፡ ጭፍራ ፡ ልከተል ፡ ሲሄድ ፡ ወደ ፡ ላይ
ያልታወቀውን ፡ ክብር
ያልታሰበውን ፡ ነገር
የተስፋውንም ፡ ምድር
ላገኝ ፡ በሰማይ

የደመና ፡ ዓምድ ፡ የእሣት ፡ ግለትም
ውኃ ፡ የሚሰጠን ፡ ሕያው ፡ ዓለትም
ዘወትር ፡ ሊመሩ ፡ ይከተሉናል
ያን ፡ ቅዱሥም ፡ ዓለት
ብታየው ፡ በዕምነት
ለሞቱቱ ፡ ሕይወት
ሊሰጥ ፡ ይችላል

ያ ፡ ዓለትም ፡ ክርስቶስ ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው
ያነፃንም ፡ ደም ፡ የወጣበት ፡ ውሃው
የኃጢአታችን ፡ ሥርየት ፡ አለነ
በአንዱ ፡ በኢየሱስ
ያ ፡ ጻድቅ ፣ ያ ፡ ቅዱስ
ለምስኪን ፣ ለርኩስ
መድኃኒት ፡ ሆነ

በሰይጣን ፡ ስጨነቅ ፡ ሲበዛብኝ ፡ ድካም
መድኃኒቴ ፡ ሆነ ፡ የልቤ ፡ ሰላም
በመስቀሉ ፡ ሞተ ፡ ለሁሉ ፡ ኃጥአን
ለሁሉም ፡ ከሞተ
ሁላችንም ፡ ሞትነ
ለሁሉም ፡ ከሞተ
ተገኘ ፡ መዳን

በአምላኬ ፡ ፊት ፡ በደለኛ ፡ ስሆን
በኢየሱስ ፡ ብገኝ ፡ ማን ፡ ይከሰኝ ፡ ይሆን?
በኢየሱስ ፡ በልጁ ፡ የጸደቅሁ ፡ ነኝ
በእርሱም ፡ ሲያየኝ
አንድ ፡ ርኩሰትም ፡ የለኝ
ሥምረቱ ፡ ግን ፡ አለኝ
በኢየሱስ ፡ ስገኝ

ይህም ፡ የብፅዕና ፡ መያዣዬ ፡ ነው
የኢየሱሥም ፡ ፅድቅ ፡ መጸናናቴ ፡ ነው
ያነገብሁት ፡ ጋሻም ፣ የደፋሁት ፡ ቁር
መድኃኒቴ ፡ ሳለ
ረድዔት ፡ ዘወትር ፡ አለ
መድኃኒቴ ፡ ሳለ
በተስፋ ፡ ልኑር

ኦ! ኢየሱስ ፡ ያልተውኸነ ፡ እስከ ፡ አሁን
መታመንህ ፡ ብቻ ፡ ተስፋችን ፡ ይሁን
ተሸከመን ፣ ጋርደን ፣ ከኛም ፡ዘንድ ፡ ሁን
አሜን! ለዘለዓለም
ምሥጋና ፡ ስብሐትም
ለአምላክ ፡ ለበጉም
ሳይጨረስ ፡ ይሁን