ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (Barkotehen Quter Zengu Atehun)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (፫x)

ከኀጢአት ፡ እርሾ ፡ ከዓለም ፡ እርኩሰት
አምልጦ ፡ ወጥቶ ፡ ታጥቦ ፡ መደሰት
የሕይወት ፡ ትርጉም ፡ በጌታ ፡ ማግኘት
እንዴት ፡ ይረሳል ፡ በጊዜው ፡ ርዝመት

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (፫x)

ሰው ፡ ያልተረዳው ፡ የችግር ፡ እሳት
ነፍሴን ፡ በግለት ፡ ሲለበልባት
ስሙ ፡ ተጠርቶ ፡ የጌታ ፡ ኢየሱስ
እንዴት ፡ ይረሳል ፡ ድኖ ፡ መተንፈስ

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (፫x)

ያለፈው ፡ ዘመን ፡ ያ ፡ የፍሰሐው
የሆሳዕናው ፡ የሃሌሉያው
ጭንቀት ፡ ሲከበን ፡ እንደ ፡ ደመና
እንዴት ፡ ይረሳል ፡ በዚህ ፡ ፈተና

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (፫x)

ይህም ፡ ቢሆን ፡ አስብ ፡ ጌታህን
በመንፈስ ፡ ሞልቶ ፡ ያዘለለህን
ከአልጋ ፡ ቁራኛ ፡ በፈውስ ፡ ያየህን
ሕይወቱን ፡ ሰጥቶ ፡ ሰው ፡ ያረገህን

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዝንጉ ፡ አትሁን (፫x)