ባርኮትህን ፡ ቁጠር (Barkotehen Quter)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

በሕይወት ፡ ማዕበል ፡ ጐርፍ ፡ ስትቀጠቀጥ
ሁሉም ፡ ጠፍቶብህ ፡ ተስፋህም ፡ ሊቆረጥ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
ወዲያው ፡ ታስባለህ ፡ ያምላክን ፡ ሥራ

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በየተራ ፡ አይተህ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘብ ፡ የእርሱን ፡ ሥራ
ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘበው ፡ ያምላክን ፡ ሥራ

በከባድ ፡ ሸክም ፡ ተጭነሃል ፡ ወይ?
የጥሪውስ ፡ መስቀል ፡ ከበደብህ ፡ ወይ?
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ጥርጥር ፡ ይብረር
በዘመንህ ፡ ሁሉ ፡ በደስታ ፡ ዘምር

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በየተራ ፡ አይተህ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘብ ፡ የእርሱን ፡ ሥራ
ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘበው ፡ ያምላክን ፡ ሥራ

ወደ ፡ ሌሎችም ፡ ሃብት ፡ ስትመለከት
አስብ ፡ የክርስቶስን ፡ ባለጸግነት
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ አይገዛውም ፡ ሃብት
የአንተንም ፡ ነፍስ ፡ ዋጋ ፡ በሰማዩ ፡ ቤት

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በየተራ ፡ አይተህ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘብ ፡ የእርሱን ፡ ሥራ
ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘበው ፡ ያምላክን ፡ ሥራ

ትልቅም ፡ ቢሆን ፡ ትንሽ ፡ ጭንቅ ፡ መከራ
ተስፋ ፡ ላትቆርጥ ፡ አምላክህን ፡ ጥራ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ መላዕክት ፡ ይስሙት
ለጉዞህም ፡ ብርታት ፡ ይስጡህ ፡ መጽናናት

አዝ፦ ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በየተራ ፡ አይተህ
ባርኮትህን ፡ ቁጠር ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘብ ፡ የእርሱን ፡ ሥራ
ባርኮትህን ፡ ዘርዝር ፡ በተራ
አይተህ ፡ ተገንዘበው ፡ ያምላክን ፡ ሥራ