በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ (Bante Tamenhugn Gieta Eyesusie)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ዋሴ
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ጨለማው ፡ በራ
ሸለቆው ፡ ሞልቶ ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ተመስገን ፡ አልኩኝ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ በድል ፡ አረፍኩኝ

በዐይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ ስትሸከመኝ
ኃይልና ፡ ብርታት ፡ ጉልበት ፡ ስትሆነኝ
የማይቻለው ፡ በአንተ ፡ ተችሎ
ዛሬም ፡ ቆሜያለሁ ፡ ጠላት ፡ ተጥሎ

አዝ፦ በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ዋሴ
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ጨለማው ፡ በራ
ሸለቆው ፡ ሞልቶ ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ተመስገን ፡ አልኩኝ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ በድል ፡ አረፍኩኝ

የማይገፋው ፡ ታላቅ ፡ ተራራ
ሲያዩት ፡ ከሩቅ ፡ እጅግ ፡ የሚያስፈራ
አንተ ፡ ስታዘው ፡ ይሆናል ፡ ሜዳ
ውሃም ፡ ያፈልቃል ፡ በምድረ ፡ በዳ

አዝ፦ በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ዋሴ
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ጨለማው ፡ በራ
ሸለቆው ፡ ሞልቶ ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ተመስገን ፡ አልኩኝ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ በድል ፡ አረፍኩኝ

ሆኖ ፡ ሲታየኝ ፡ ሁሉ ፡ ጨለማ
የማይቃና ፡ ፍፁም ፡ ጠማማ
ስምህን ፡ ጠራሁ ፡ ተስፋዬን ፡ ይዤ
ዘምበል ፡ አልክልኝ ፡ ኢየሱስ ፡ አጋዤ

አዝ፦ በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ዋሴ
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ጨለማው ፡ በራ
ሸለቆው ፡ ሞልቶ ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ተመስገን ፡ አልኩኝ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ በድል ፡ አረፍኩኝ

እረዳት ፡ አጋዥ ፡ ተስፋ ፡ ለሌለው
የጠላት ፡ ጩኸት ፡ ላደናቆረው
የፍቅር ፡ ድምጽህን ፡ ታሰማዋለህ
ጽኑ ፡ ምሽግ ፡ ነህ ፡ ታሳርፋለህ

አዝ፦ በአንተ ፡ ታመንሁኝ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱሴ
በሕይወት ፡ ዘመኔ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ዋሴ
ስምህን ፡ ስጠራ ፡ ጨለማው ፡ በራ
ሸለቆው ፡ ሞልቶ ፡ ሆነ ፡ ተራራ
ተመስገን ፡ አልኩኝ ፡ መዝሙር ፡ ዘመርኩኝ
በአምላኬ ፡ ጥላ ፡ በድል ፡ አረፍኩኝ