ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ (Bamlakie Tamegnie Qeterun Ezelalehu)

From WikiMezmur: Mezmur Lyrics
Jump to: navigation, search

አዝ፦ ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ልዑል ፡ በቀኜ ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ
ጉልበቴ ፡ ነውና ፡ ሁሉን ፡ እረታለሁ

ማዳን ፡ በማይችሉ ፡ ነፍሴ ፡ መች ፡ ታመነች
የኢየሱስን ፡ ማዳን ፡ ደጋግማ ፡ አይታለች
መከራው ፡ ሲያካፋ ፡ ሲወርድ ፡ እንደጤዛ
ተከልዬ ፡ አመለጥኩ ፡ በዘለዓለም ፡ ቤዛ

አዝ፦ ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ልዑል ፡ በቀኜ ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ
ጉልበቴ ፡ ነውና ፡ ሁሉን ፡ እረታለሁ

ከተለጠጠው ፡ ቀስት ፡ መድህኔ ፡ ጋርዶኛል
ከተሰበቀው ፡ ጦር ፡ እርሱ ፡ ሰውሮኛል
ልቤን ፡ አሳረፈው ፡ ዐይኔንም ፡ ከእንባ
በመጽናናት ፡ ሞላኝ ፡ በድል ፡ እንድገባ

አዝ፦ ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ልዑል ፡ በቀኜ ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ
ጉልበቴ ፡ ነውና ፡ ሁሉን ፡ እረታለሁ

ሞቴን ፡ ሲጠብቁ ፡ በሕይወት ፡ አኖረኝ
ቁስሌንም ፡ አክሞ ፡ መድሃኒት ፡ ሆነልኝ
በኃያላንም ፡ ላይ ፡ ስለእኔ ፡ ወረደ
ቅዱሳን ፡ ሲጐዱ ፡ መች ፡ አይቶ ፡ ወደደ

አዝ፦ ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ልዑል ፡ በቀኜ ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ
ጉልበቴ ፡ ነውና ፡ ሁሉን ፡ እረታለሁ

በመከራዬ ፡ ቀን ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ከሆነ
ታላቁንም ፡ ማዳን ፡ ካሳየኝም ፡ ለእኔ
ረጅም ፡ ዕድሜ ፡ ጌታ ፡ ያጠግበኛል
ጐልማሳነቴንም ፡ እንደነስር ፡ ያድሰዋል

አዝ፦ ባምላኬ ፡ ታምኜ ፡ ቅጥሩን ፡ እዘላለሁ
ልዑል ፡ በቀኜ ፡ ነው ፡ ለምን ፡ እሠጋለሁ
ጉልበቴ ፡ ነውና ፡ ሁሉን ፡ እረታለሁ